1. ይህን የአባልነት መመሪያ ቅጽ በአማርኛ ወይንም በእንግሊዝኛ መሙላት ይችላሉ
2. አንዴ በጀመሩበት ቋንቋ ቅጹን መሙላትዎን ይቀጥሉ
3. ፎቶግራፍዎን በሚያስገቡበት ግዜ የፎቶው መጠን እና ቅርጽ አራት ማዕዘን ካሬ ወይን 1×1 Aspect Ratio እንዲኖረው ያድርጉ
4. የአባልነት ክፍያዎን በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003508785 ባሉበት ሆነው ማስገባት ይችላሉ
5. ዝቅተኛው ዓመታዊ የመደበኛ አባልነት ክፍያ 120 ብር ነው
6. ዝቅተኛው ዓመታዊ የታዳጊ አባልነት ክፍያ 12 ብር ነው
7. ክፍያዎን በባንካችን ሂሳብ ቁጥር ሲያስተላልፉ ምክኒያት የሚለው ቦታ ላይ ሙሉ ስምዎን በእንግሊዝኛ መጻፍ ይኖርብዎታል።
8. ዲጂታል የአባልነት መታወቂያዎ እርስዎ ክፍያ ከፈጸሙበት ሰዓት ጀምሮ በሚቆጠር 24 ሰዓት ውስጥ በኢሜይልዎ ይደርስዎታል።
9. የታተመ የአባልነት መታወቂያ ከፈለጉ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ በአካል በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
10. የዓመታዊ የአባልነት ክፍያው የታተመ የአባልነት መታወቂያ ማሳተሚያ ክፍያን አይጨምርም